top of page
Website design 1.jpg
Search

የሐዘን መልዕክት

Updated: Feb 23

ከ አንድነት ለአማራ ኀልውና ትግል (አንድነት)


በታሪካዊውና የአባቶቻችን ርስት በሆነው የሸዋ ምድር፣ በምንጃር አውራጃ፣ ሸንኮራ አረርቲ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመታደም በተገኙ ምዕመናን ላይ በደረሰው ያልታሰበ አደጋ ከልብ አዝነናል፡፡


በግንባታ ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን እየጎበኙ የነበሩ ወገኖቻችን የእንጨት ርብራቡ ተደርምሶ በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወገናችን ደግሞ የአካል ጉዳት እዳጋጠመው አረጋግጠናል፡


በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ፈጣሪ ነብሳቸውን ይማርልን!


ለሁሉም ተጎጅ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን!


የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ደግሞ ፈውስን እንመኛለን!!


አንድነት ለአማራ ኀልውና ትግል (አንድነት)


መስከረም 21/2018 ዓ.ም.


 
 
 

Comments


bottom of page