ከአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት እዝ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
- Amhara Andnet
- Oct 7, 2025
- 4 min read
▬▬▬▬▬
"የወጣንለትን አላማ እንጠብቃለን ፤ የሕዝባችንና የሰራዊታችንን አሁናዊ ፍላጎት እንፈፅማለን"
"ሴረኞችን እናጋልጣለን፤ ሴራን እናከሸፋለን"
የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት በአፓርታይዳዊ አገዛዝ የወደቀ በደም እና በአጥንት በገነባት ሀገሩ የመኖር ተፈጥሯዊ መብቶ ተነጥቆ ሀገርን እንመራለን በሚሉ የዱርዮ ስብስቦች እረፍት አልባ እና ተሳዳጅ ሆኗል። ሕዝባችንን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ በመሆነ መልኩ በተለይ ከጣሊያን ወረራ ማግሰት መንግስት መር ጥቃት ከፍ ብሎም የዘር ማጥፋት ወንጀል በአገዛዞች እብሪት ተፈፅሞበታል።
የአማራ ሕዝብ በሀገር ስም በተቀመጡ ጠባብ ብሄርተኞች ላለፉት ግማሽ ምዕተ አመት አማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ዘርፈ ብዙ ጥቃቶች ተካሂዶበታል። ሕዝባችንም ለዘመናት የተፈራረቁበትን በርካታ መከራና ፍዳዎች በሰላምም በአፈሙዝም ታግሏል። አሁን ላይ የሀገራችንም ፤ የሕዝባችንም ነቀረሳ የሆነው የብልፅግናው አገዛዝ ከዚህ ቀደም በህዝባችን ላይ ያልተደረጉ፤ ይደረጋሉም ተብለው የማይታሰቡ ግፎች ፈፅሞበታል። በዚህም በሕዝባችን ላይ መንግስት መር የዘር ማጥፋት ወንጀል(State sponsored genocide) በየጊዜው በተፈራረቁ ገዥዎች።
በሕዝባችን ላይ ያንዣበበውን የመጥፋት አደጋ በውሉ በመረዳት ከሶስት ክረምት በላይ መራራ የደም ዋጋ የአማራ ፋኖ እየከፈለ ይገኛል።
የአማራ ህዝብ የሕልውና ትግል ለባለፉት አመታት ወጥ የሆነ ሕግ ደንብ እና መመሪያ መርህ ያልተዘጋጀለት እንዲሁም በተለምዷዊ ጀብደኝነት መመራቱ አሁን ላለንበት ምስቅልቅል ዳርጎናል። የሕዝብን ትግል በስውር አላማ እና አጀንዳ አለፍ ሲልም አሁናዊ ተቀዳሚ ጠላቶቻችን የደም ዋጋ የተከፈለለትን ትግል አሳልፎ ለመስጠት ያሰፈሰፉ እጆችን በጥንቃቄ መቁረጥ ያስፈልጋል።
የአማራ ፋኖ በተለይ እንደነዚህ ባሉ በተደበላለቁ ፍላጎቶች እንዲታመስ ያደረገው ውስጣዊ አንድነትን እንደ ስትራቴጂካዊ ግብ ሳይሆን እንደ ትርፍ ማየቱ ነዉ ብለን እናምናለን። በዚህም የአማራ ፋኖ ከመነቋቆር ወጥቶ ማዕከላዊነት የተከበረበት አማራዊ አንድነት መስራት እንዳለበት እናምናለን። የአማራ ፋኖ አመራርም ይሁን አባል ይሄን ለመስራት ከይሉኝታ እና ከፍርሀት ቆፈን መላቀቅ አለበት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ተፈጥሯዊ ፀጋ የሆኑት አርቆ አሳቢነትና አስተዋይነት መጠቀምና መፈፀም ትግሉን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ወሳኝ እርምጃ ነው። ይህን ስናደርግ በጠላት ላይ ፖለቲካዊውም ይሁን ወታደራዊ የበላይነትን እንወስዳለን።
የአማራ ሕዝብ የማሸነፊያ ቁልፍም ይሄ ብቻ መሆኑን አውቀን አንድነትን በፍጥነት እና ባስቸኳይ መስራት ይኖርብናል። አንድነትን ከላይ ወደ ታች መስራት የማይቻል ከሆነ የሕዝባችንን ስቃይና መከራ ለማሳጠር እንዲሁም የወጣንለትን ግብ እና አላማ ለማሳካት ከታች ወደ ላይ ለመስራት ሁሉም ታጋይ ቁርጠኛ እንዲሆን እናሳስባለን።
የአማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል ጫፍ ለማድረስም ይሁን በዘላቂነት ወደትግል የወጣንባቸው ጥያቄዎች ሳይሸራረፉ እንዲመለሱ ለማድረግ ቢቻል ከጠላት በላይ አደረጃጀት መስራት ካልሆነ ደግሞ የማይደፈር እና ተገዳዳሪ ኋይል መፍጠር ያስፈልጋል። ትግሉን የምናሻግረው በጠላቶቻችን ልክ ሕግ ፣ ደንብ ፣ስርዓት እና መዋቅር ሰርተን መሆን ይኖርበታል ብለን እናምናለን። አገዛዙም ይሁን የአማራ ታሪካዊ ጠላቶች ሕዝባችንን ስርዓታዊና መዋቅራዊ በሆነ መልኩ ሲያሳድዱት እንደኖሩ ሁሉ እኛም ለሕዝባችን የሚመጥን አደረጃጀት መስራት ይጠበቅብናል። በዚህም እንደ ወሎ በርካታ አኩሪና ፈር ቀዳጅ እንዲሁም ዘመን አይሽሬ ጀብዱዎችን በከበረ መስዕዋትነት ፈፅመናል። እንደ አብነት በ2015ዓ/ም ከተደረጉ ጀብዱዎች መካካል፦
ሀ. በሰሜን ሸዋ በተጀመረው የስርዓቱን አገልጋይ ካድሬዎች ምንጠራ የተሳተፍን ስንሆን በዚህም የአማራ ክልል ብልፅግና ፅ/ቤት ኋላፊን አቶ ግርማ የሸጥላ እስከ ወዳኛው በመሸኘት ለአማራዊያን የይቻላል መንፈስን ማጎናፀፍ ችለናል።
ለ. ሰኔ 14, 2015 ዓ/ም በአማራ ፋኖ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በደላንታ ወረዳ ውስጥ-አምባ ቁጭብላ ቀበሌ የጠላትን ሀይል ሙሉ በሙሉ በወገን በኩል ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ደምስሰናል። በዙም ቀን ለብዙ አማራውያን ምሳሌ የሆነውን የመጀመሪያ ከተማን(ወገልጤናን) ተቆጣጠርን።
ሐ. ሰኔ 22, 2015ዓ/ም በጉባላፍቶ ወረዳ 028 ቀበሌ ልዩ ስሙ ኩረታ በተባለ ቦታ ጠላት አድማ ብተናን እና መከላከያን በመደምሰስ ታሪክ ሰርተናል። በዚህ ውጊያ በጠላት በኩል እጅግ በጣም ብዙ ሰብዓዊውም ቁሳዊውም ጉዳት ሲደርስ ለአማራነታቸው በነፃ ለነፃነት የገበርንበት ቀን መሆኑ መቼም አንረሳውም።
መ. ሀምሌ 24, 2015ዓ.ም ሳንቃ ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ በርካታ የጠላት ሀይልን ድባቅ የመታንበት መሆኑ
ሠ. ሀምሌ 29, 2015ዓ.ም ጋሸና ቦያ ሀሙሲት በወቅቱ ላስታ አሳምነው ክ/ጦር ጋር በመጣመር አኩሪ ጀብዱ ፈፅመናል።
እንደ አብነት በመጀመሪያ የሕልውና ትግሉ አመት የጠቀስናቸው አበይት አውደ ውጊያዎች ቢሆኑም በርካታ ታሪኮችን መስራታችንን ጠላትም ወገንም ያውቀዋል። በአባታችን አርበኛ ኮ/ል ፈንታሁን ሙሃባው እየተመራን የጠላትን አከርካሪ ላለፉት መራራ የትግል አመታት በፅናት ቆይተናል። ነገር ግን አብዛኛውን የወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት እዝ አመራሮችም ይሁን የሰራዊት አባላት እኛ በምንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ቢሆኑም ለአለፉት ሶስት ወራት ግን ከውስጥም ከውጭም የሚደረግ ድጋፍ እየደረሰን እንዳልሆነ ለመላው ደጋፊዎቻቸው ማሳወቅ እንፈልጋለን። ችግሩ እንዲፈታም በትዕግስት እና በብስለት ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ አመራሮች ብናሳውቅም ሊፈታልን ባለመቻሉ ይህንን ባለአራት ነጥብ የአቋም መግለጫ እንድናወጣ ተገደናል።
1. በሀገር ውስጥም በሀገር ውጭም ላሉ ደጋፊዎቻችን፦
የአማራ ሕዝብ ትግል ሁሉም አማራ በአቅሙ ልክ እና በሚችለው አግባብ እየታገለ ነው ብለን እናምናለን። በዚህ ትግል የደጋፊዎቻችን ሚና ጉልህ እና አይተኬ ነው። ነገር ግን የምትልኩት ገንዘብ በትክክል መሬት ላይ ላለው ታጋይ አታጋይ መድረሱን ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ከመስከረም 21, 2018ዓ.ም ጀምሮ እኛ በምናሳውቃችሁ ግብረ ሀይል በኩል ድጋፍ እንድታደርጉልን ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።
2. ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አመራሮች፦
ድርጅታችን አፋህድ የአሰራር መዋቅሮችን ዘርግቶ ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን እና እስከአሁን ድረስ በእዛችን በኩል የደረሱ ምስቅልቅሎችን እንዲሁም በተፈጠረው የአሰራር ግልፀኝነት ምክኒያት እንዲመረምር እና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ በጥብቅ እናሳስባለን። ከዚህ በተጨማሪ የደም ዋጋ የከፈልንለት ድርጅታችን አፋህድ ራሱን ከሰርጎ ገብ የትግል ጠላፊ ጩልሌዎች እንዲጠብቅና እንዲያፀዳ ጭምር እናሳስባለን። ድርጅታችን አፋህድን በእጅ አዙር በመጠምዘዝ የተከፈለውን የህይወት ዋጋ ደመ ከልብ ለማድረግና ለተቀዳሚ ጠላታችን አሳልፎ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ግልፅ እንቅስቃሴ በድርጅታዊ መርህና አሰራር በአስቸኳይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ በሰፊው የአማራ ሕዝብ ስም እንጠይቃለን።
3. ለአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኋይል አመራር እና አባላትበመጀመሪያ ከሰሞኑ በወሎ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው አፋብኋ ምኒልክ እዝ ለፈፀማቸው አኩሪ ድሎች ትልቅ ክብር የምንሰጠውና የታሪኩም አካል በመሆናችን በእጅጉ እንኮራለን። በመሆኑም እንደ አማራ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ የተመሰረተ አንድ ወጥ እና አታጋይ ድርጅት ስለሚያስፈልገን ለአንድነት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ትኩረት እንድትሰጡ በቆሰሉት እና በተሰውት የትግሉ ሰማዕታት ስም እንጠይቃለን።
4. ለሚድያ አካላቶች
እኛ ለሕዝባችን ታምነን አንድያ ነፍሳችንን ለመስዕዋትነት ያቀረብን መሆናችንን አውቃችሁ መፈራረጁን ፤ መጠላለፉን ለሕዝባችንም ለትግሉም ክብር ስትሉ እንድታቆሙ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን። ይህ ትግል የህይወት ዋጋ የሚከፈልለት መሆኑን አውቃችሁ ለትግሉ የሚጠቅመውንና ትግሉን የሚያሻግረውን የአርበኝነት ስራ እንድትሰሩ ጭምር እናሳስባለን።
በመጨረሻም የአማራ ሕዝብ ትግል በልኩ እና በውል አላማዎቹን እና ግቦቹን እንዲመታ በቁርጠኝነት የምንሰራ መሆኑን እናሳውቃለን። እኛ ለአማራ ፋኖ አንድነት ሰንኮፍ የሆኑትን ጉዳዮች መርምረን ለይተን አውቀን እየጣልን የመጣን ለወደፊትም ከሕዝባችን ጥቅም ከወጣንለት አላማ በታች ባሉ ሁሉም ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ዝግጁ እና ደስተኞች መሆናችንን ጭምር ለመላው አማራ እናሳውቃለን። የሕዝባችንንም ይሁን የሰራዊታችን ተቀዳሚ አላማ የሆነው አንድነትን ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናችንን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን። በወሎ ቀጠናም ይሁን በመላው አማራ ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጋዮች ጋር ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በንግግር ለመፍታት እንዲሁም ፍፁም ስህተት የሆነውን ጥቁር ደም መቃባታ የማንፈልግ እና አንድም አፈሙዝ ወደ ወገን የማናዞር መሆናችንን ሁሉም አማራ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!!
ክብር እና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!!
መስከረም 21, 2018ዓ.ም




Comments